ስለ ባዶሓደ

አእምሮወችን በማገናኘት፣ የእውቀት አድማስን ማስፋት

ዓለም አቀፍ የቋንቋ ክፍተትን ማጥበብ

በዚህ በቋንቋ በተከፋፈለ መረጃ በተሞላ ዓለም ውስጥ፣ እኛ ከፍተኛ ጥራት ያለው የቴክኒክ እውቀትን አፋችሁን በፈታችሁበት ቋንቋ በእጃችሁ መዳፍ ውስጥ ለማስገባት፣ በቋንቋችሁ እና በቴክኒክ ትምህርታችሁ መሃል ልክ እንደ አንድ የሚያስተሳስር ድልድይ ሁነን ቆመናል።

የእኛ ማንነት

ባዶሓደ ስም ብቻ ሳይሆን ከዛ በላይ የኛ የቃል ኪዳናችን ነው። ከአማርኛ ”0” እና ከትግርኛ ”1” ከተባሉ አሃዞች ተወስዶ የተጣመረው፣ እንዲሁም የዲጂታል ቋንቋ መሰረት የሆነውን የምርት መለያችን ስም ማለት ባዶሓደ፣ ልክ እንደ ስሙ በቴክኖሎጂ ትምህርት ላይ የቴክኖሎጂ ትምህርትን ለማንኛውም ህብረተሰብ ለማዳረስ ወደ ሁሉ ቦታ ጉዞ መጀመሩን ያሳያል። እኛ ርዴት እና ፈጠራ በቋንቋ ብቻ ተወስኖ መቅረት የለበትም የሚል እምነት አለን። ለዚህም ነው እጅግ አስፈላጊ የሆኑትን የቴክኒክ መጻሕፍት ከእንግሊዘኛ ወደ አማርኛ፣ ትግርኛ እና ሌሎችንም ወደ ብዙ ቋንቋዎች ለመተርጎም እራሳችንን አሳልፈን የሰጠነው።

የእኛ ተልዕኮ

ተልዕኳችን ቀላል ሆኖም ግን ጥልቅ ነው፤ "ቋንቋን በሚያካትት የቴክኖሎጂ ትምህርት አማካኝነት በዓለም ዙሪያ እውቀትን ማበልጸግ።" በዚህ በፍጥነት በማደግ ላይ ባለው የዲጂታል ዘመን፣ ቋንቋ በሚፈጥራቸው መሰናክሎች ምክንያት ማንም ሰው ወደኋላ እንደማይቀር ከወዲሁ እናረጋግጣለን። ሰፊ የሆኑ የቴክኒክ እውቀት ማከማቻ መዳረሻወችን በነጻ በመስጠት፣ አፋችሁን በፋታችሁበት ቋንቋ መማሩን እውን ብቻ ሳይሆን አስደሳች ተሞክሮም እንዲሆን እናደርጋለን።

የእኛ አቀራረብ

  1. ጥራት ያላቸው ትርጉሞች፤ እኛ አንድ በሙያው የተካኑ የተርጓሚዎች ቡድን ሲኖረን እንዲሁም ከደራሲዎች እና ከቴክኖሎጅ ባለሙያዎች ጋርም በቅርበት እንሰራለን። ይህም ትርጉሞቻችን ትክክለኛ፣ ማለት ባህላቸውን የጠበቁ እና መጽሐፎቹ ሲፈጠሩ የተጻፉበትን ይዘት የጠበቁ መሆናቸውን ያረጋግጥልናል።
  2. ለተጠቃሚ ምቹ የሆነ መዋቅር፤ ድረገጻችን ለተደራሽነት እና ለአጠቃቀም ቀላል እንዲሆን ተደርጎ የተነደፈ ነው። ይህም እናንተ ቴክኖሎጂን የማወቅ ጉጉት ያለው እና ለቴክኖሎጂ አዲስ ሰው ወይም በቴክኖሎጂ ልምድ ያለው ባለሙያ ብትሆኑም፣ በመረጣችሁት ቋንቋ ይዘት መፈለግን እና ከይዘቱ ጋር መሳተፉን ቀላል ያደርገዋል።
  3. ቅድሚያ ለማህበረሰቡ፤ እኛ ማህበረሰቡ ባለው ሃይል ላይ እናምናለን። በእኛ መዋቅር በኩል ተጠቃሚዎች፣ ደራሲዎች እና የቴክኖሎጂ አድናቂዎች እውቀትን ለመጋራት፣ ለመማር እና ለማደግ ይገናኛሉ። እኛም በአንድነት የእውቀት እና የፈጠራ ድንበሮችን ገፍተን መጣል እንደምንችል በማመን ይህንን መስተጋብር እናበረታታለን።
  4. ዘላቂነት እና ኃላፊነት፤ የእኛ ቁርጠኝነት ከትምህርት ባሻገር ይዘልቃል። የእኛ መጽሐፍቶችን መጀመሪያ-በዲጂታል አቀራረብ ማቅረብ የሚለው ስልታችን ዘላቂነት ካላቸው ግቦችችን ጋር እጅ ለእጅ ይሄዳል፣ ይሄ አካይዳችንም ተለምዷዊ ከሆነው የመጽሃፍ ህትመት ጋር የተያያዘውን የአካባቢ ተጽእኖ ይቀንሳል።
  5. ፈጠራ እና ዝግመተ ለውጥ: የቴክኖሎጂው አለም ዝም ብሎ ባለበት አይቆምም እኛም እንደዛው። ተደራሽ በሆነ የቴክኖሎጂ ትምህርት ላይ ግንባር ቀደም መሆናችንን ለማረጋገጥ፣ መዋቅራችንን እና አቅርቦታችንን ለማሻሻል አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እና የዘመኑ አዲስ መጤ የሆኑ ነገሮችን በየጊዜው ባለማቋረጥ እንመረምራለን።

አብራችሁን ተጓዙ

እኛ ባዶሓደወች በቋንቋወች እና በቴክኖሎጅ መጽሐፍቶች ላይ ያሉትን ዕንቅፋቶችን ማፍረስ ላይ ብቻ የተገታን ሳንሆን፤ እውቀት ራሱ የእውቀት ወሰንን የማያደርግበትን የወደፊቱን ጊዜ አሁን በመገንባት ላይ እንገኛለን። የስራችሁን ተደራሽነት ለማስፋት የምትፈልጉ ደራሲ ብትሆኑም ወይም ወደ ቴክኖሎጂ ውቅያኖስ ውስጥ ጠልቃችሁ ለመግባት የጓጓችሁ አዲስ የቴክኖሎጅ ተማሪወች ወይም ለትምህርት ፍትሃዊነት ራሳችሁን አሳልፋችሁ የሰጣችሁ አጋሮችን ማለት በጠቅላላ ሁላችሁንም ከእኛ መአድ ጋር እንድትሳተፉ እንጋብዛችኋለን።

ሁላችንም አንድ ላይ በመሆን ሁሉም ሰው በዚህ የዲጂታል ዘመን የመማር፣ የማደግ እና እንዲሁም ስኬታማ ሰው የመሆን ዕድል የሚያገኝበትን ዓለም መፍጠር እንችላለን። ባዶሓደ፣ ቴክኖሎጂ ወደ ልዕልና በሚሄድበት ጉዞ ውስጥ በቋንቋ አንድ የሚያደርገን ቦታ ነው።

Connecting Minds, Expanding Horizons

Bridging the Global Knowledge Divide

Badohade is a pioneering platform where technology education transcends traditional barriers. In a world teeming with information, yet divided by language, we stand as a unifying force, bringing high-quality technical knowledge to your fingertips in your native tongue.

Our Essence

Badohade is more than just a name; it is a promise! Derived from the Amharic and Tigrigna words for "0" and "1," the foundations of digital language, our brand symbolizes the beginning of a journey in technology education for everyone, everywhere. We believe that understanding and innovating should not be confined. That is why we are dedicated to translating the world's most essential technical books into a multitude of languages—from English and Spanish to Chinese, Arabic, Amharic, and Tigrigna.

Our Mission

Our mission is simple: "Empower global minds through language-inclusive technology education." In this rapidly evolving digital era, we ensure that no one is left behind. We provide free access to a vast repository of technical knowledge, allowing learning in your native language to not only be a reality, but a delightful experience.

How We Do It

  1. Quality Translations: We have a team of expert translators, and we collaborate closely with authors and technical experts. This ensures that our translations are accurate, culturally sensitive, and maintain the essence of the original texts.
  2. User-Friendly Platform: Our website is designed for accessibility and ease of use. Whether you are a seasoned technology professional or a curious beginner, finding and engaging with content in your preferred language is a breeze.
  3. Community at the Core: We believe in the power of community. Through our platform, users, authors, and technology enthusiasts come together to share, learn, and grow. We encourage this interaction, because we believe that— together—we can push the boundaries of knowledge and innovation.
  4. Sustainability and Responsibility: We are committed to more than just education. Our digital-first approach aligns with sustainability goals that reduce the environmental impact associated with traditional publishing.
  5. Innovation and Adaptation: The technology world does not stand still, and neither do we. We continuously explore emerging technologies and trends to enhance our platform and offerings, ensuring that we remain at the forefront of accessible technical education.

Join Our Journey

At Badohade, we are not just dissolving barriers; we are building futures where knowledge knows no bounds. Whether you are an author looking to broaden the reach of your work, a a learner eager to dive into new technology realms, or a partner committed to educational equity—we invite you to join us!

Together we can create a world where everyone has the opportunity to learn, grow, and succeed in the digital age.

Badohade - Where Language Unites in the Pursuit of Technological Mastery.