የሩቢ ኦንሬይልስ ስልጠና

በሩቢ ኦን ሬይልስ ስልጠና ውስጥ ትኩረት የሚሰጠው፣ በየትኛውም ቴክኖሎጂ ላይ ጠቃሚ በሚሆኑ አጠቃላይ ችሎታዎች ላይ ነው፡፡ አንዴ የድር አፕልኬሽኖች እንዴት እንደሚሰሩ ካወቃችሁ በኋላ፣ ሌሎች መዋቅሮችን ለመማር የምታጠፉት ጊዜ በጣም አጪር ይሆናል፡፡ ለዚህ ስልጠና የሩቢ ኦን ሬይልስ መዋቅርን የመረጥን ቢሆንም፣ ድር ማበልጸግን ለመማር፣ ምንም የተሻለ መዋቅር ኑሮ አያውቅም፡፡

ሩቢ ፕሮግራም ቋንቋን፣ የዩኒክስ የማዘዥያ መስመርን፣ ሃ.ጽ.መ.ቋን (HTML)፣ የወ.ሉ.ቅን (CSS)፣ አነስተኛ ጃቫስክሪፕትን እና ተ.መ.ቋን (SQL) ጨምሮ የተዘጋጀው መጽሐፍን ለመማር፣ ምንም ዓይነት መደበኛ ቅድመ ዝግጅት አያስፈልግም፡፡ ያን ለመረዳት ብዙ ይዘት ቢኖረውም፣ አፕልኬሽን ለማበልጸግ አዲስ ለሆኑ ሰዎች ግን በቂ ተማርን በተለይ ደግሞ በበማዘዥያ መስመር ላይ መሰረታዊ እውቀትን ለማግኘት የሚያስፈልገውን ትምህርት ተማር እና በሩቢ ላይ መሰረታዊ እውቀትን ለማግኘት የሚያስፈልገውን ተማር በሚለው ስልጠና እንዲጀምሩ ይመከራል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ እጅግ በርካታ የሆኑ፣ ፍጹም አዲስ ጀማሪዎች ይህንን ስልጠና በብቃት ተወጥተውታል፤ ስለዚህ እናንተም እንደነሱ የድር አፕልኬሽኖችን ለመገንባት ጓጉታችሁ ከሆነ፣ በዚህ ምክር ላስተጓጉላችሁ አልፈልግም፡፡

የዚህ ስልጠና ዋናው የማስተማሪያ ዘዴ ተከታታይ የሆኑ ምሳሌዎችን በመጠቀም፣ ርቀትን በመጨመር፣ በትክክል የሚሰራ አፕልኬሽንን መገንባት ነው። አንድ አነስተኛ በሆነ ማለት ሰላምታ በተባለ አፕልኬሽን በመጀመር፣ ከዚያም በጥቂቱ ብቃት ያለው አንድ ጨዋታ የተባለ አፕልኬሽንን መገንባት እና መጨረሻ ላይ ደግሞ አንድ ማሳያ የተባለ እውነተኛ አፕልኬሽንን መገንባት ይሆናል፡፡ አጠቃላይ የወል ስማቸው እንደሚያመለክተው፣ እነዚህ አፕልኬሽኖች ተግባራዊ በሆነ መልኩ፣ ለማንኛውም የድር አፕልኬሽን ተግባራዊ በሚሆኑ አጠቃላይ መርሆዎች ላይ ያተኩራሉ፡፡ በተለይ ምዕራፍ 14 ላይ የበለጸገው፣ የተሞላው ማሳያ የተባለው አፕልኬሽን የተጠቃሚ መመዝገቢያን፣ መግቢያን እና የመለያ አስተዳደርን ጨምሮ አንድ የበለጸገ የድር አፕልኬሽን የሚያስፈልጉትን ዋና ዋና ገጸባህሪያትን ሁሉ ያካትታል። በተጨማሪም ቁልጪ ብሎ የትዊተር የድርጣቢያን ከመምሰሉ ባሻገር፣ ብዙ ነገሮችን ይዟል/ይገልጻል፤ እንደ አጋጣሚ ሁኖ ትዊተር መጀመሪያ የተገነባውም በሬይልስ ነበረ።

እንጀምር!

የእንግሊዝኛው የሩቢ ኦን ሬይልስ ስልጠና መጽሐፍ በኤሌክትሮኒክ መጽሐፍ ማለት በፒዲኤፍ (PDF)፣ በኢፐብ (EPUB) እና ኤምኦቢአይ (MOBI) መልኩ በበቂ ተማር ላይ በግዢ ይገኛል። ተጓዳኙ የቪዲዮ ተከታታይ ትምህርት አስራ አራት ክፍሎች ሲኖሩት እያንዳንዱ የቪድዮው ትምህርት ደግሞ የእያንዳንዱን የመጽሐፍ ምዕራፍ ይሸፍናል።