መሰናክሎችን በማፍረስ፣ የወደፊቱን መገንባት

ቋንቋ በቴክኖሎጂ ትምህርት ውስጥ አንድ ከሚሆንበት ባዶሓደ ጋር ተዋወቁ። እውቀት በቀላሉ ለሁሉ የሚዳረስበትን መንገድ ለመለወጥ፣ የቋንቋ ገደብን ለመሻገር እና ቴክኖሎጂ ለሁሉም ሰው እንደ አንድ ዓለም አቀፋዊ ቋንቋ የሚሆነበትን የወደፊት ጊዜ ለመቅረጽ ከኛ ጎን ተሰለፉ።

ሁሉን መጽሓፍቶች ይቃኙ ተጨማሪ መረጃ ያግኙ ↓

Dissolving Barriers, Building Futures

Discover Badohade, where language unites technology education! Join us in transforming access to knowledge, transcending linguist barriers, and creating a future where technology is a universal language.

Discover all books Learn more ↓
ድንበር አልባ የቴክኖሎጂ ትምህርት

እንኳን ወደ ባዶሓደ በደህና መጡ

በቴክኖሎጂ ትምህርት መልክአምድር ላይ በማደግ ላይ ወዳለው ባዶሓደ እንኳን በደህና መጡ። አዲስ ነገርን የምናስተዋውቅ እና ታታሪ ኩባንያ እንደመሆናችን መጠን፣ ቴክኖሎጂን በመማር ላይ ያሉ የቋንቋ መሰናክሎችን ለማፍረስ ቆርጠን ተነስተናል። ጉዞአችንንም በአማርኛ ተናጋሪው ህብረተሰብ ጀምረነዋል።

የመጀመሪያ የመሰረት ድንጋያችን

በማይክል ሃርትል የተጻፈውን “የሩቢ ኦን ሬይልስ ስልጠና” ን እና በሊ ዶናሆ፣ በኒክ ሜርዊን እና እንዲሁም በማይክል ሃርትል የተጻፈውን ​"በማበልጸጊያ አካባቢ ላይ መሰረታዊ እውቀትን ለማግኘት የሚያስፈልገውን ተማር" ን ማለት ለዚሁ የትርጎማ ስራችን እንደ የመሰረት ድንጋይ መሰረት የጣሉ ሁለት መጽሓፎችን በአማርኛ ተርጉመን ለንባብ በማብቃታችን እጅጉን ደስተኞች ነን። ሁለቱም መጽሓፎች ሙያው በተመሰከረለት መልኩ ወደ አማርኛ የተተርጎሙ ብቻ ሳይሆኑ፣ እንዲሁም የጉዟችን ጅምሬ ምልክት እና ደረጃውን የጠበቀ የቴክኖሎጂ ትምህርትን ለአማርኛ ተናጋሪዎች ለማድረስ ያለንን ቁርጠኝነት የሚያሳዩ ናቸው።

ለተጠቃሚወች ምቹ የሆኑ የመስመር ላይ ትምህርቶች

የእኛ የትምህርት ምንጮች በድረገጻኛችን በኩል ተደራሾች እና ለተጠቃሚወች ምቹ የሆነ የእውቀት ገበታን ለማቅረብ የተዘጋጁ የመስመር ላይ ትምህርቶች ናቸው። ይህ አካሄድም እንደ ፒዲኤፍ (PDF)፣ ኢፐብ (EPUB) ወይም ኪንድል የመሳሰሉ የተለያዩ የዲጅታል ቅርጸቶችን ማውረድ ሳያስፈልግ ወቅታዊ እና በቀላሉ ተደራሽ የሆነ የቴክኖሎጂ እውቀት የማቅረብ ራዕያችን ጋር ይስማማል።

ራዕያችን ከአድማስ ባሻገር ያለፈ ነው

መጽሐፍ ተርጉሞ ማቅረቡን በአማርኛ የጀመርን ቢሆንም እንኳ፣ ራዕያችን ግን ከአንድ ቋንቋ ባሻገር ያለፈ ሰፊ የሆነ የትርጉም አድማስን ያካተተ ነው። የምሳሌነት አድማሳችንን የበለጠ በማስፋት፣ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ትግርኛን ጨምሮ በሌሎች ቋንቋዎችም በርካታ የሆኑ የቴክኒክ መጻሕፍትን ተርጉመን ለማቅረብ አቅደናል። የባህላዊ ቋንቋ ድንበሮችን በማፍረስ የቴክኖሎጂ ትምህርትን ሁለንተናዊ የሆነ አንድ ቋንቋ ለማድረግ ቆርጠን ተነስተናል።

ለምን ባዶሓደ’ን ምርጫችሁ ታደርጉታላችሁ?

እኛ ባዶሓደወች አንድ የቴክኖሎጅ መጽሓፍቶችን የሚተረጉም መዋቅር ብቻ ሳንሆን፣ እኛ አንድ የለውጥ እንቅስቃሴም ጪምር ነን። ቴክኖሎጂ እና ትምህርት፡ በእያንዳንዱ ህብረተሰብ ላይ በሚያመጡት ጠቃሚ ብልጽግና እና ለውጥ ላይ ይሄ ነው የማይባል እምነት አለን፣ እናም ያንን ብልጽግና እና ለውጥ ለሁሉም ህብረተሰብ ተደራሽ ይሆን ዘንድ ትጥቃችንን ታጥቀን ቆርጠን ተነስተናል። ባዶሓደ’ን ምርጫችሁ በምታደርጉበት ጊዜ፣ ቴክኖሎጂን ብቻ መማር ሳይሆን ለእድገት፣ ሁሉን ህብረተሰብ ለማካተት እና የቋንቋ መሰናክሎችን ከነ አንካቴው ለማፍረስ ቁርጠኛ ከሆነውን ማህበረሰብ ጋር እየተቀላቀላችሁ ጪምርም ነው፡ ማለት ነው።

የጉዞ አጋራችን ሁኑ

ከእኛ ጋር አብራችሁን እያደጋችሁ እንድትሄዱ በትህትና እንጋብዛችኋለን። እናንተ የቴክኖሎጂ አፍቃሪ፣ ወይም ቴክኖሎጂን የማወቅ ጉጉት ያለው እና ለቴክኖሎጂ አዲስ ሰው ወይም በቴክኖሎጂ ልምድ ያለው ባለሙያ ብትሆኑም፣ ባዶሓደ በቴክኖሎጂ ላይ ለምታደርጉት አዲስ የቴክኖሎጂ ግኝት ጉዞ ላይ የጉዞ አጋራችሁ ነው። የቴክኖሎጂ ትምህርትን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ሁሉን ህብረተሰብ የሚያካትት ለማድረግ፣ ተጨማሪ ቋንቋዎችን እና የቴክኒክ ትምህርት ምንጮችን ስለምንጨምር ተከታተሉን።

"ባዶሓደ ቴክኖሎጂ ከቋንቋ ጋር የሚቆራኝበት እና የዕድሎች ዓለም የሚፈጠርበት መድረክ ነው።"
Tech Education Without Borders

Welcome to Badohade

Welcome to Badohade, a rising star in tech education! As an innovative and energetic startup, we are invested in dissolving linguistic barriers in technology education, beginning with the rich and diverse Amharic-speaking community.

Our First Milestones

We have proudly launched with two foundational texts: "Ruby on Rails Tutorial," authored by Michael Hartl, and "Learn Enough Dev Environment to Be Dangerous," co-authored by Michael Hartl, Lee Donahoe, and Nick Merwin. Both texts have been expertly translated into Amharic, which marked the beginning of our journey and symbolized our commitment to bringing world-class technology education to Amharic speakers.

Tailored for Your Online Learning Experience

Our resources are curated for online learning, providing an accessible and interactive experience directly from our website. This method aligns with our vision to deliver up-to- date, easily accessible technology knowledge without the need for downloads in various formats like PDF, EPUB, or Kindle.

Looking Ahead: Expanding Horizons

While we have begun with Amharic, our vision encompasses a broader horizon. In the near future, we will introduce a wealth of technical texts in other languages, including Tigrigna, further widening the scope of our reach. We are committed to transforming technology education into a universal language.

Why Choose Badohade?

At Badohade, we are not just a platform; we are a movement! We believe in the transformative power of technology, education, and community, and we are dedicated to extending that power to all through easy access.


By choosing Badohade, you are not just learning technology. You are also joining a community committed to growth, inclusivity, and dissolving barriers of language and power.

Join Us on This Revolutionary Journey

As we grow, we invite you to grow with us. Whether you are a technology enthusiast, a curious beginner, or a seasoned professional, Badohade seeks to be your companion in the journey of technological discovery. Stay tuned as we continue to add more languages and resources, making technology education more inclusive than ever before.

"Badohade: Where Technology Meets Language, Creating Worlds of Possibilities."
Explore all books

ሁሉን መጽሓፍቶች ይቃኙ

የሩቢ ኦን ሬይልስ ስልጠና

እንኳን ወደ ሩቢ ኦን ሬይልስ ስልጠና በደህና መጣችሁ! የዚህ ስልጠና አላማ አንድ ብጁ የድር አፕልኬሽን እንዴት እንደሚበለጸግ ማስተማር ነው፡፡ ከስልጠናው የምታገኙት ችሎታ፣ በድር አበልጻጊነት ሙያ ስራ ለማግኘት፣ እንደ ግል ኮንትራት ሰራተኛ ሁኖ ለመስራት፣ ወይም የራሳችሁ የሆነ አንድ ድርጅት ለመክፈት የሚያስችል ትልቅ እድልን ይከፍትላችኋል። የድር አፕልኬሽኖች እንዴት እንደሚበለጸጉ የምታውቁ ከሆነ ደግሞ፣ ይህ ስልጠና ከሩቢ ኦን ሬይልስ ጋር በፍጥነት እንድትተዋዎቁ ያግዛችኋል። የሩቢ ኦን ሬይልስ ስልጠና መጽሐፍ ማለት እንደ ጊትሃብ፣ ሁሉ፣ ሾፒፋይ እና ኤርቢኤንቢ ያሉ ታዋቂ ድረገጾች በስተጀርባ ሁኖ የሚያገለግለውን ክፍተ ምንጩን የድር መዋቀር ማለት ሩቢ ኦን ሬይልስን በመጠቀም በስራ ላይ የሚውሉ አመርቂ የድር አፕልኬሽኖችን እንዴት እንደምታበለጽጉ እና እንዴት እንደምታሰማሩ ያስተምራችኋል። እንዲሁም የተካነ የድር ማበልጸግ አሰራር ላይ የተሟላ ግንዛቤ እንዲኖራችሁ ለማረጋገጥ፤ የላቁ የሬይልስ ርዕሶችንም ይዳስሳል።

Ruby on Rails Tutorial

Welcome to the Ruby on Rails Tutorial! The purpose of this tutorial is to teach you how to develop custom web applications. The resulting skillset will put you in a great position to get a job as a web developer, start a career as a freelancer, or found a company of your own. If you already know how to develop web applications, this tutorial will quickly get you up to speed with Ruby on Rails. The Ruby on Rails Tutorial book instructs you in developing and deploying robust, industrial-strength web applications with Ruby on Rails, the open-source web framework behind major sites like GitHub, Hulu, Shopify, and Airbnb. It also explores advanced Rails topics to ensure you gain a thorough understanding of professional web development practices.

በማበልጸጊያ አካባቢ ላይ መሰረታዊ እውቀትን ለማግኘት የሚያስፈልገውን ተማር

ለማንኛውም ፍላጎት ላለው ገንቢ (ወይም በአጠቃላይ ቴክኒካዊ ለሆነ ሰው) በጣም አስፈላጊ ከሆኑት ተግባራት መካከል አንዱ ኮምፒዩተራቸውን ልክ እንደ አንድ የማበልጸጊያ አካባቢ በማቀናበር የድር ጣቢያዎችን፣ የድር አፕልኬሽኖችን እና ሌሎች ሶፍትዌሮችን ለማበልጸግ ተስማሚ እንዲሆን ማድረግ ነው። በማበልጸጊያ አካባቢ ላይ መሰረታዊ እውቀትን ለማግኘት የሚያስፈልገውን ተማር፣ ሁሉንም አስፈላጊ ቁሳቁሶች በአንድ ቦታ ላይ በማስቀመጥ ዋናውን የበቂ ተማር ተከታታይ የስልጠና ትምህርትን እና የሩቢ ኦን ሬይልስ ስልጠናን ለማሟላት የተቀየሰ ነው።

Learn Enough Dev Environment to Be Dangerous

One of the most important tasks for any aspiring developer—or any technical person generally—is setting up their computer as a development environment, making it suitable for developing websites, web applications, and other software. Learn Enough Dev Environment to Be Dangerous is designed to complement the main Learn Enough sequence and the Ruby on Rails Tutorial by putting all of the relevant material in one place.